!
ስንክሳር ማለት የእግዚአብሔርን ረድኤት አጋዥ በማድረግ በበጎ ስጦታውም የተሰበሰበ ማለት ነው።
ይህ ሃይማኖቶታቸው የቀና የከበሩ አባቶች ፣ ከቅዱሳን ሰማዕታት ፣ ከጻድቃን ፣ ከነቢያት ፣ ከሐዋርያት ፣ ከሊቃነ ጳጳሳት ፣ ከኤጲስቆጶሳት ፣ ከመነኮሳትም ሁሉ ከገዳማውያንም ከገድሎቻቸው ከመላእከት አለቆችም ከድርሳናቸው የሰበሰቡትና ያቀነባበሩት አምላክን የወለደች እመቤታችን የከበረች ድንግል ማርያም ከአደረገቻቸው ድንቆች ተአምራቶችም የክብር ባለቤት የሆነ የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የበዓላቶቹን መታሰቢያ እስከ ዓመቱ ፍፃሜ ሁል ጊዜ ምእመናን እንዲያነቡት እንዲሰሙትም ይሆን ዘንድ ተዘጋጀ።
ይህንንም ቅዱስ መጽሐፍ ሰብስበው ያቀነባበሩት በሽህ ሦስት መቶ ንጹሐን በሆኑ ሰማዕታት ዘመን ነው። የእሊህ የተባረኩ አባቶቻችን ጸሎታቸውና በረከታቸው ከእኛ ጋር ይኑር።
!!
የቅዱሳንን ታሪክ ለማንበብ ከታሪካቸውም ለመማር እኛም በክርስትና ህይወታችን እንዲሁም በእለት ተእለት የኑሮ እንቅስቃሴያችን ውስጥ በዋነኝነት ቅዱሳኑ እንዲራዱን እንዲያማልዱንም በሌላም መልኩ ከነሱ የክርስትና ህይወት በመነሳት እኛስ ምን ማረግ እንችላለን ከቅዱሳኑ ታሪክ ምንን እማራለው የሚለውን እንድናስብ ይረዳናል ብሎ በማሰብ እንዲሁም በብዙ መፅሃፈ ስንክሳርን ማግኘት በማይችሉ ምእመናን ጥያቄ መሰረት እንዲሁም ከጉዋደኞቾ ፣ ቤተሰቦቾ ፣ የስራ ባልደረቦቾ ባጠቃላይ ከወዳጅ ዘመዶቾ ጋር በመሆን ይጠቀሙበት ዘንድ ትልቁን የቤተክርስቲያን መፅሃፍ መፅሃፈ ስንክሳርን ጠቅለንም ፈጣሪ በፈቀደ የቻልነውን የቻልነውን ሙሉውን ታሪክ ደግሞ ዋና ታሪኩን ጨምቀን አቅርበናል።
እርሶም እኝህን መንፈሳዊ ታሮኮች ሰአት መድበው በቀን ቢያንስ ከ3—10 ደቂቃ ወስደው የእለቱን ስንክሳር እንዲያነቡ እንዲማሩበት ከወዳጆቾ ጋርም ውይይቶችን እኒዲያረጉበት እንመክራለን።
በዚህ አፕሊኬሽን ውስጥ የተካተቱት ብዙሃኑ ቅዱሳን ከ እህታማማች እምነት ተከታይ አብያተ ክርስትያናት ናቸው
እነዚህም አብያተ-ክርስትያናት:-
- የ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
- የ ግብፅ / አሌክሳንድርያ ኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
- የ ሶሪያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
- የ አርመንያ ሐዋርያዊ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
- የ ኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
- የ ህንድ - ማንካራ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን
ያንብቡ ያነበቡትንም ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር በመሆን ይወያዩበት - አፕሊኬሽኑንም ለሌላቸው ያካፍሉዋቸው
አስተያየትዎ አይለየን
ከቅዱሳኑ ይደምረን
!!
በዚህ እለት ? ከነ ታሪካቸው ገብተው ይመልከቱ ከበረከታቸውም ተካፋይ ይሁኑ። ይህንንም ስራ ሰርቶ ለማጠናቀቅ አመታትን የፈጀ ሲሆን በዚህ ስራ ላይ አብዛኞቹን ፅሁፎቹን በማዘጋጀት የላቀ ሚና ለተገበረው ለዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ምስጋናችን ከልብ ነው።
ዲ/ን ዮርዳኖስም ለብዙ አመታት እድሜውን ሙሉ መንፈስ ቅዱስ ባቀበለው መጠን ጎንደር በሚገኘዉ በዝክረ ቅዱሳን ጉባኤ የቅዱሳን ታሪክ በመማር ፣ ፣ ፣ በመተርጎም ፣ በመፃፍ ፣ በማዘጋጀት እና በማስተማር ጭምር የኖረ የቤተክርስቲያናችን አገልጋይ ነው። ይህንንም እርሱ ያዘጋጃቸውን ፅሁፎች በነፃ ምዕመንን ለማስተማር በፌስ ቡክ ፣ በቴሌ ግራም እንዲሁም ለኛም በነፃ ሰጥቶን እኛም ዘመኑን በሚዋጅ መልኩ ክርስቲያኑን ለማስተማር እና እና የቅዱሳን በረከትንም ላንባቢውም እንድንካፈል በአፕሊኬሽን መልክ አቅርበናል።
ስንክሳር * Sinksar - (Życie świętych) w języku amharskim i angielskim.
ስንክሳር(የቅዱሳን ታሪክ) ዘ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ Sinksar(Synaksarium) Cerkiew Prawosławna Tewahedo
W imię Ojca, Syna i Ducha Świętego, Bóg Jedyny Amen!
Aby uczyć się z Synaksarium lub historii i Żywotów Świętych Chrześcijan i poprawić swoje chrześcijaństwo, szczególnie w życiu Kościoła prawosławnego Tewahedo, gorąco polecamy przeczytanie książki, a tym z Was, którzy nie mieli dostępu do książki tutaj to aplikacja, która zawiera główne historie ze zdjęciami ilustrującymi historię.
Większość świętych pochodzi z Wschodniego Kościoła Prawosławnego.
Ta wschodnia wspólnota prawosławna składa się z sześciu autokefalicznych kościołów:
- Etiopski Kościół Prawosławny Tewahedo,
- Koptyjski Kościół Prawosławny Aleksandrii,
- Syryjski Kościół Prawosławny w Antiochii,
- Ormiański Kościół Apostolski,
- Erytrejski Kościół Prawosławny Tewahedo oraz
- Syryjski Kościół Prawosławny Malankara.
- W językach amharskim i angielskim.
Czytaj dalej, dyskutuj o tym, co przeczytałeś z innymi chrześcijanami i udostępniaj aplikację wszystkim chrześcijanom na świecie.
Ostatnia aktualizacja
24 sty 2024