በገና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዜማ መሳሪያ ሲሆን በዋናነት ለመለኮታዊ የእግዚአብሔር ፈቃድ ማስፈጸሚያ ማለትም ለምስጋናና ለልመና የሚያገለግል ነው። በገና ከብሉይ ኪዳን የመጀመሪያ መጽሐፍ ከኦሪት ዘፍጥረት እስከ መጨረሻው የአዲስ ኪዳን መጽሐፍ ዮሐንስ ራእይ ድረስ አገልግሎቱ የተጠቀሰ እጅግ ድንቅ መንፈሳዊ የዜማ መሳሪያ ነው። የዚህ መተግበሪያ ዋና ዓላማ በገና ለሚደረድሩ እንዲሁም ለሚማሩ በቀላሉ በርካታ መዝሙሮችን ቁጥራቸውን ቅኝታቸውን በማግኘት እግዚአብሔርን በበገና እንዲያመሰግኑ እንዲሁም እንዲለማመዱ ነው።
በተጨማሪም ክራር ለሚለማመዱ በቁጥር የተቀመጠ መለማመጃ ስለሌለ የበገና መዝሙሮችን ቁጥራቸውን ለክራር እንዲያመች በማድረግ በመቀየር መሠረታዊ ልምምድ ማድረግ ለሚፈልጉ እንዲያግዝ የክራር ቁጥርም አካቶ ይዟል።